የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 8:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 ሀብት እንድታፈራ ኃይል የሰጠህ አምላክህ ይሖዋ መሆኑን አስታውስ፤+ ይህን ያደረገው ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ለአባቶችህ በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ለመፈጸም ነው።+

  • ዘዳግም 28:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ይሖዋ በምድርህ ላይ በወቅቱ ዝናብን ለማዝነብና የእጅህን ሥራ ሁሉ ለመባረክ ሲል መልካም የሆነውን ጎተራውን ይኸውም ሰማይን ይከፍትልሃል።+ አንተም ለብዙ ብሔራት ታበድራለህ፤ አንተ ግን አትበደርም።+

  • 2 ዜና መዋዕል 1:11, 12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ከዚያም አምላክ ሰለሞንን እንዲህ አለው፦ “የልብህ መሻት ይህ ስለሆነ ደግሞም ብልጽግና፣ ሀብትና ክብር ወይም የሚጠሉህን ሰዎች ሞት* አሊያም ረጅም ዕድሜ* ስላልተመኘህ፣ ይልቁንም አንተን ንጉሥ አድርጌ የሾምኩበትን ሕዝቤን ማስተዳደር እንድትችል ጥበብና እውቀት ስለጠየቅክ፣+ 12 ጥበብና እውቀት ይሰጥሃል፤ ከዚህም ሌላ ከአንተ በፊት የነበረ ማንኛውም ንጉሥ ያላገኘውን፣ ከአንተም በኋላ የሚነሳ የትኛውም ንጉሥ የማያገኘውን ብልጽግና፣ ሀብትና ክብር እሰጥሃለሁ።”+

  • ኢዮብ 42:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 በመሆኑም ይሖዋ ከፊተኛው የኢዮብ ሕይወት ይልቅ የኋለኛውን አብዝቶ ባረከ፤+ ኢዮብም 14,000 በጎች፣ 6,000 ግመሎች፣ 1,000 ጥማድ ከብቶችና 1,000 እንስት አህዮች አገኘ።+

  • ምሳሌ 10:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 የይሖዋ በረከት ባለጸጋ ታደርጋለች፤+

      እሱም ከበረከቱ ጋር ሥቃይን* አይጨምርም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ