ምሳሌ 3:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 ይሖዋ የክፉውን ቤት ይረግማል፤+የጻድቁን መኖሪያ ግን ይባርካል።+ ምሳሌ 10:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 የይሖዋ በረከት ባለጸጋ ታደርጋለች፤+እሱም ከበረከቱ ጋር ሥቃይን* አይጨምርም። ዕብራውያን 11:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በተጨማሪም ያለእምነት አምላክን በሚገባ ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ አምላክ የሚቀርብ ሁሉ እሱ መኖሩንና ከልብ ለሚፈልጉትም ወሮታ ከፋይ መሆኑን ማመን ይኖርበታልና።+ ያዕቆብ 5:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እነሆ፣ የጸኑትን ደስተኞች* እንደሆኑ አድርገን እንቆጥራቸዋለን።+ ስለ ኢዮብ ጽናት ሰምታችኋል፤+ በውጤቱም ይሖዋ* ያደረገለትን አይታችኋል፤+ በዚህም ይሖዋ* እጅግ አፍቃሪና* መሐሪ እንደሆነ ተመልክታችኋል።+
6 በተጨማሪም ያለእምነት አምላክን በሚገባ ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ አምላክ የሚቀርብ ሁሉ እሱ መኖሩንና ከልብ ለሚፈልጉትም ወሮታ ከፋይ መሆኑን ማመን ይኖርበታልና።+
11 እነሆ፣ የጸኑትን ደስተኞች* እንደሆኑ አድርገን እንቆጥራቸዋለን።+ ስለ ኢዮብ ጽናት ሰምታችኋል፤+ በውጤቱም ይሖዋ* ያደረገለትን አይታችኋል፤+ በዚህም ይሖዋ* እጅግ አፍቃሪና* መሐሪ እንደሆነ ተመልክታችኋል።+