1 ሳሙኤል 18:10, 11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በማግስቱም ከአምላክ የመጣ መጥፎ መንፈስ ሳኦልን ያዘው፤+ ዳዊት በፊት እንደሚያደርገው ሁሉ በገና እየደረደረ+ ሳለ ሳኦል ቤቱ ውስጥ እንግዳ ባሕርይ ያሳይ* ጀመር። ሳኦልም በእጁ ጦር ይዞ ነበር፤+ 11 እሱም ‘ዳዊትን ከግድግዳው ጋር አጣብቀዋለሁ!’ ብሎ በማሰብ ጦሩን በኃይል ወረወረው።+ ዳዊት ግን ሁለት ጊዜ ከእሱ አመለጠ። 1 ሳሙኤል 20:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ከዚያም ዳዊት በራማ ከምትገኘው ከናዮት ሸሸ። ሆኖም ወደ ዮናታን መጥቶ “ምን አደረግኩ?+ የፈጸምኩትስ በደል ምንድን ነው? አባትህ ሕይወቴን* ለማጥፋት የሚፈልገው በእሱ ላይ ምን ኃጢአት ሠርቼ ነው?” አለው። 1 ሳሙኤል 20:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 በዚህ ጊዜ ሳኦል እሱን ለመግደል ጦሩን ወረወረበት፤+ ስለሆነም ዮናታን አባቱ፣ ዳዊትን ለመግደል ቆርጦ መነሳቱን አወቀ።+ 1 ሳሙኤል 23:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ዳዊት በሆሬሽ በሚገኘው በዚፍ ምድረ በዳ ሳለ ሳኦል የእሱን ሕይወት* ለመፈለግ መውጣቱን አውቆ* ነበር።
10 በማግስቱም ከአምላክ የመጣ መጥፎ መንፈስ ሳኦልን ያዘው፤+ ዳዊት በፊት እንደሚያደርገው ሁሉ በገና እየደረደረ+ ሳለ ሳኦል ቤቱ ውስጥ እንግዳ ባሕርይ ያሳይ* ጀመር። ሳኦልም በእጁ ጦር ይዞ ነበር፤+ 11 እሱም ‘ዳዊትን ከግድግዳው ጋር አጣብቀዋለሁ!’ ብሎ በማሰብ ጦሩን በኃይል ወረወረው።+ ዳዊት ግን ሁለት ጊዜ ከእሱ አመለጠ።
20 ከዚያም ዳዊት በራማ ከምትገኘው ከናዮት ሸሸ። ሆኖም ወደ ዮናታን መጥቶ “ምን አደረግኩ?+ የፈጸምኩትስ በደል ምንድን ነው? አባትህ ሕይወቴን* ለማጥፋት የሚፈልገው በእሱ ላይ ምን ኃጢአት ሠርቼ ነው?” አለው።