1 ሳሙኤል 22:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ዳዊትም ከዚያ ተነስቶ+ ወደ አዱላም+ ዋሻ ሸሸ። ወንድሞቹና መላው የአባቱ ቤት ይህን ሲሰሙ እሱ ወዳለበት ወደዚያ ወረዱ። 2 ችግር ያጋጠማቸው፣ ዕዳ ያለባቸውና የተከፉ* ሰዎች ሁሉ ወደ እሱ ተሰበሰቡ፤ እሱም አለቃቸው ሆነ። ከእሱም ጋር 400 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ነበሩ። 1 ሳሙኤል 27:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 በመሆኑም ዳዊት አብረውት ከነበሩት 600 ሰዎች+ ጋር ተነስቶ የጌት ንጉሥ ወደሆነው ወደ ማኦክ ልጅ ወደ አንኩስ+ ተሻገረ። 1 ዜና መዋዕል 12:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ዳዊት ከቂስ ልጅ ከሳኦል የተነሳ ተደብቆ ይኖር+ በነበረበት ጊዜ እሱ ወዳለበት ወደ ጺቅላግ+ የመጡት ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ እነሱም በጦርነት ከረዱት ኃያላን ተዋጊዎች መካከል ነበሩ።+
22 ዳዊትም ከዚያ ተነስቶ+ ወደ አዱላም+ ዋሻ ሸሸ። ወንድሞቹና መላው የአባቱ ቤት ይህን ሲሰሙ እሱ ወዳለበት ወደዚያ ወረዱ። 2 ችግር ያጋጠማቸው፣ ዕዳ ያለባቸውና የተከፉ* ሰዎች ሁሉ ወደ እሱ ተሰበሰቡ፤ እሱም አለቃቸው ሆነ። ከእሱም ጋር 400 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ነበሩ።
12 ዳዊት ከቂስ ልጅ ከሳኦል የተነሳ ተደብቆ ይኖር+ በነበረበት ጊዜ እሱ ወዳለበት ወደ ጺቅላግ+ የመጡት ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ እነሱም በጦርነት ከረዱት ኃያላን ተዋጊዎች መካከል ነበሩ።+