መሳፍንት 3:26, 27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 ኤሁድ ግን እነሱ ቆመው ሲጠባበቁ ሳለ አመለጠ፤ በተቀረጹት ምስሎች* + በኩል አድርጎም በሰላም ወደ ሰኢራ ደረሰ። 27 እዚያም እንደደረሰ በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ+ ቀንደ መለከት ነፋ፤+ እስራኤላውያንም ከተራራማው አካባቢ ወጥተው በእሱ መሪነት አብረውት ወረዱ። 2 ሳሙኤል 15:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 አቢሴሎምም “የቀንደ መለከት ድምፅ ስትሰሙ ‘አቢሴሎም በኬብሮን ነገሠ!’+ ብላችሁ አውጁ” በማለት በመላው የእስራኤል ነገዶች መካከል ሰላዮችን አሰማራ።
26 ኤሁድ ግን እነሱ ቆመው ሲጠባበቁ ሳለ አመለጠ፤ በተቀረጹት ምስሎች* + በኩል አድርጎም በሰላም ወደ ሰኢራ ደረሰ። 27 እዚያም እንደደረሰ በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ+ ቀንደ መለከት ነፋ፤+ እስራኤላውያንም ከተራራማው አካባቢ ወጥተው በእሱ መሪነት አብረውት ወረዱ።