2 ሳሙኤል 3:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 አበኔር ወደ ኬብሮን+ በተመለሰ ጊዜ ኢዮዓብ ከእሱ ጋር በግል ለመነጋገር ነጠል አድርጎ ወደ ቅጥሩ በር ይዞት ገባ። ሆኖም በዚያ ሳሉ ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው፤+ ይህን ያደረገው የወንድሙን የአሳሄልን ደም ለመበቀል ነው።+ 1 ነገሥት 2:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 “የጽሩያ ልጅ ኢዮዓብ በእኔ ላይ ያደረገውን ነገር ይኸውም በሁለቱ የእስራኤል ሠራዊት አለቆች ማለትም በኔር ልጅ በአበኔርና+ በየቴር ልጅ በአሜሳይ+ ላይ ያደረገውን በሚገባ ታውቃለህ። ይህ ሰው እነዚህን ሰዎች በመግደል ጦርነት ሳይኖር በሰላሙ ጊዜ ደም አፍስሷል፤+ እንዲሁም በወገቡ ላይ የታጠቀው ቀበቶና በእግሩ ላይ ያደረገው ጫማ በጦርነት ጊዜ በሚፈሰው ደም እንዲበከል አድርጓል።
27 አበኔር ወደ ኬብሮን+ በተመለሰ ጊዜ ኢዮዓብ ከእሱ ጋር በግል ለመነጋገር ነጠል አድርጎ ወደ ቅጥሩ በር ይዞት ገባ። ሆኖም በዚያ ሳሉ ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው፤+ ይህን ያደረገው የወንድሙን የአሳሄልን ደም ለመበቀል ነው።+
5 “የጽሩያ ልጅ ኢዮዓብ በእኔ ላይ ያደረገውን ነገር ይኸውም በሁለቱ የእስራኤል ሠራዊት አለቆች ማለትም በኔር ልጅ በአበኔርና+ በየቴር ልጅ በአሜሳይ+ ላይ ያደረገውን በሚገባ ታውቃለህ። ይህ ሰው እነዚህን ሰዎች በመግደል ጦርነት ሳይኖር በሰላሙ ጊዜ ደም አፍስሷል፤+ እንዲሁም በወገቡ ላይ የታጠቀው ቀበቶና በእግሩ ላይ ያደረገው ጫማ በጦርነት ጊዜ በሚፈሰው ደም እንዲበከል አድርጓል።