-
ኢያሱ 7:24-26አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 በኋላም ኢያሱና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ የዛራን ልጅ አካንን፣+ ብሩን፣ የክብር ልብሱን፣ ጥፍጥፍ ወርቁን፣+ ወንዶች ልጆቹን፣ ሴቶች ልጆቹን፣ በሬውን፣ አህያውን፣ መንጋውን፣ ድንኳኑንና የእሱ የሆነውን ሁሉ ወደ አኮር ሸለቆ*+ አመጡ። 25 ኢያሱም አካንን “መዓት* ያመጣህብን ለምንድን ነው?+ ይሖዋም በዛሬው ዕለት መዓት ያመጣብሃል” አለው። ከዚያም እስራኤላውያን በሙሉ በድንጋይ ወገሩት፤+ በእሳትም አቃጠሏቸው።+ በዚህ መንገድ ሁሉንም በድንጋይ ወግረው ገደሏቸው። 26 በእሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የሚታየውን የድንጋይ ቁልል ከመሩበት። በዚህ ጊዜ የይሖዋ ታላቅ ቁጣ በረደ።+ የዚያ ቦታ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር* ሸለቆ የሚባለው በዚህ የተነሳ ነው።
-