መዝሙር 18:7-12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ምድርም ትንቀጠቀጥና ትናወጥ ጀመር፤+የተራሮች መሠረቶች ተንቀጠቀጡ፤እሱ ስለተቆጣም ራዱ።+ 8 ከአፍንጫው ጭስ ወጣ፤የሚባላም እሳት ከአፉ ወጣ፤+ፍምም ከእሱ ፈለቀ። 9 ወደ ታች ሲወርድ ሰማያት እንዲያጎነብሱ አደረገ፤+ከእግሮቹም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበር።+ 10 በኪሩብ ላይ ተቀምጦ እየበረረ መጣ።+ በመንፈስ* ክንፎች በፍጥነት ወረደ።+ 11 ከዚያም በጨለማ ራሱን ሸፈነ፤+ጥቁር ውኃና ጥቅጥቅ ያለ ደመና+እንደ መጠለያ በዙሪያው ነበር። 12 በፊቱ ካለው ብርሃን፣ከደመናቱ መካከል በረዶና ፍም ወጣ። መዝሙር 77:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 የነጎድጓድህ ድምፅ+ እንደ ሠረገላ ድምፅ ነበር፤የመብረቅ ብልጭታዎች በዓለም* ላይ አበሩ፤+ምድር ተናወጠች፤ ደግሞም ተንቀጠቀጠች።+
7 ምድርም ትንቀጠቀጥና ትናወጥ ጀመር፤+የተራሮች መሠረቶች ተንቀጠቀጡ፤እሱ ስለተቆጣም ራዱ።+ 8 ከአፍንጫው ጭስ ወጣ፤የሚባላም እሳት ከአፉ ወጣ፤+ፍምም ከእሱ ፈለቀ። 9 ወደ ታች ሲወርድ ሰማያት እንዲያጎነብሱ አደረገ፤+ከእግሮቹም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበር።+ 10 በኪሩብ ላይ ተቀምጦ እየበረረ መጣ።+ በመንፈስ* ክንፎች በፍጥነት ወረደ።+ 11 ከዚያም በጨለማ ራሱን ሸፈነ፤+ጥቁር ውኃና ጥቅጥቅ ያለ ደመና+እንደ መጠለያ በዙሪያው ነበር። 12 በፊቱ ካለው ብርሃን፣ከደመናቱ መካከል በረዶና ፍም ወጣ።