-
1 ዜና መዋዕል 11:22-25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 የዮዳሄ ልጅ በናያህ+ በቃብጽኤል+ ብዙ ጀብዱ የፈጸመ ደፋር ሰው* ነበር። እሱም የሞዓቡን የአርዔልን ሁለት ወንዶች ልጆች ገደለ፤ እንዲሁም በረዶ በሚጥልበት ዕለት ወደ አንድ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ወርዶ አንበሳ ገደለ።+ 23 ደግሞም ቁመቱ አምስት ክንድ* የሆነ እጅግ ግዙፍ+ ግብፃዊ ገደለ። ግብፃዊው የሸማኔ መጠቅለያ+ የሚመስል ጦር በእጁ ይዞ የነበረ ቢሆንም በትር ብቻ ይዞ በመግጠም የግብፃዊውን ጦር ከእጁ ቀምቶ በገዛ ጦሩ ገደለው።+ 24 የዮዳሄ ልጅ በናያህ ያደረጋቸው ነገሮች እነዚህ ነበሩ፤ እሱም እንደ ሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎች ዝነኛ ነበር። 25 ከሠላሳዎቹም ይበልጥ ታዋቂ የነበረ ቢሆንም የሦስቱን ሰዎች ያህል ማዕረግ አላገኘም።+ ይሁን እንጂ ዳዊት የራሱ የክብር ዘብ አለቃ አድርጎ ሾመው።
-
-
ምሳሌ 30:30አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 ከአራዊት ሁሉ ኃያል የሆነውና
ማንንም አይቶ ወደ ኋላ የማይመለሰው አንበሳ፣+
-