-
ዘኁልቁ 23:24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ልክ እንደ አንበሳ የሚነሳው ሕዝብ ይህ ነው፤
እሱም እንደ አንበሳ ተነስቶ ይቆማል።+
ያደነውን እስኪበላ፣
የተገደሉትንም ደማቸውን እስኪጠጣ ድረስ አይተኛም።”
-
-
ኢሳይያስ 31:4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ይሖዋ እንዲህ ብሎኛልና፦
“አንበሳ ይኸውም ደቦል አንበሳ ባደነው እንስሳ ላይ ቆሞ እንደሚያገሳ፣
ብዙ እረኞች ተጠራርተው ሲመጡበትም
ጩኸታቸው እንደማያሸብረው፣
የሚያሰሙትም ሁካታ እንደማያስፈራው ሁሉ
የሠራዊት ጌታ ይሖዋም ለጽዮን ተራራና ለኮረብታዋ ሲል
ለመዋጋት ይወርዳል።
-