31 ከዚያም ንጉሡ እንዲህ አለው፦ “በል ልክ እንዳለው አድርግ፤ ግደለውና ቅበረው፤ ኢዮዓብ አላግባብ ካፈሰሰውም ደም እኔንና የአባቴን ቤት አንጻ።+ 32 ኢዮዓብ አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ከእሱ ይልቅ ጻድቅና የተሻሉ የነበሩትን ሁለት ሰዎች ማለትም የእስራኤል ሠራዊት አለቃ+ የነበረውን የኔርን ልጅ አበኔርንና+ የይሁዳ ሠራዊት አለቃ+ የነበረውን የየቴርን ልጅ አሜሳይን+ በሰይፍ መትቶ በመግደሉ ይሖዋ ደሙን በራሱ ላይ ይመልስበታል።