-
ነህምያ 13:25-27አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 ስለሆነም ገሠጽኳቸው፤ እርግማንም አወረድኩባቸው፤ አንዳንዶቹንም መታኋቸው፤+ ፀጉራቸውንም ነጨሁ፤ እንዲሁም እንደሚከተለው በማለት በአምላክ አስማልኳቸው፦ “ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው መስጠት የለባችሁም፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁም ሆነ ለራሳችሁ መውሰድ የለባችሁም።+ 26 የእስራኤል ንጉሥ ሰለሞን ኃጢአት የሠራው በእነሱ ምክንያት አይደለም? በብዙ ብሔራት መካከል እንደ እሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም፤+ ደግሞም በአምላኩ ዘንድ የተወደደ+ ስለነበር አምላክ በመላው እስራኤል ላይ ንጉሥ አደረገው። ይሁንና ባዕዳን ሚስቶች እሱን እንኳ ኃጢአት እንዲሠራ አደረጉት።+ 27 እናንተም ባዕዳን ሴቶችን በማግባት በአምላካችን ላይ ታማኝነት የጎደለው ተግባር ፈጸማችሁ፤ ታዲያ እንዲህ ያለውን ተሰምቶ የማያውቅ እጅግ መጥፎ ድርጊት እንዴት ትፈጽማላችሁ?”+
-