1 ዜና መዋዕል 29:23-25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ሰለሞንም በአባቱ በዳዊት ፋንታ በይሖዋ ዙፋን+ ላይ ንጉሥ ሆኖ ተቀመጠ፤ እሱም ተሳካለት፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ታዘዙለት። 24 መኳንንቱና+ ኃያላን ተዋጊዎቹ+ ሁሉ እንዲሁም የንጉሥ ዳዊት ወንዶች ልጆች+ ሁሉ ለንጉሥ ሰለሞን ተገዙለት። 25 ይሖዋም በእስራኤል ሁሉ ፊት ሰለሞንን እጅግ ታላቅ አደረገው፤ ደግሞም በእስራኤል ከእሱ በፊት የነበሩት ነገሥታት ያላገኙትን ንጉሣዊ ግርማ አጎናጸፈው።+ መዝሙር 72:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ፀሐይ ብርሃኗን እስከሰጠች፣ጨረቃም በሰማይ ላይ እስካለች ድረስ፣ከትውልድ እስከ ትውልድ+ አንተን ይፈሩሃል።
23 ሰለሞንም በአባቱ በዳዊት ፋንታ በይሖዋ ዙፋን+ ላይ ንጉሥ ሆኖ ተቀመጠ፤ እሱም ተሳካለት፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ታዘዙለት። 24 መኳንንቱና+ ኃያላን ተዋጊዎቹ+ ሁሉ እንዲሁም የንጉሥ ዳዊት ወንዶች ልጆች+ ሁሉ ለንጉሥ ሰለሞን ተገዙለት። 25 ይሖዋም በእስራኤል ሁሉ ፊት ሰለሞንን እጅግ ታላቅ አደረገው፤ ደግሞም በእስራኤል ከእሱ በፊት የነበሩት ነገሥታት ያላገኙትን ንጉሣዊ ግርማ አጎናጸፈው።+