-
1 ነገሥት 10:24-26አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 የምድር ሕዝቦችም ሁሉ አምላክ በሰለሞን ልብ ውስጥ ያኖረውን ጥበብ+ ይሰሙ ዘንድ ከእሱ ጋር ለመገናኘት ይጓጉ ነበር።* 25 ወደ እሱ የሚመጡትም ሰዎች በየዓመቱ የብር ዕቃዎች፣ የወርቅ ዕቃዎች፣ ልብሶች፣ የጦር ትጥቆች፣ የበለሳን ዘይት፣ ፈረሶችና በቅሎዎች ስጦታ አድርገው ያመጡ ነበር።
26 ሰለሞንም ሠረገሎችንና ፈረሶችን* መሰብሰቡን ቀጠለ፤ እሱም 1,400 ሠረገሎችና 12,000 ፈረሶች*+ ነበሩት፤ እነሱንም በሠረገላ ከተሞችና በኢየሩሳሌም በንጉሡ አቅራቢያ አኖራቸው።+
-
-
2 ዜና መዋዕል 1:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ከግብፅ የሚመጣው እያንዳንዱ ሠረገላ 600 የብር ሰቅል ያወጣ ነበር፤ አንድ ፈረስ ደግሞ 150 ሰቅል ያወጣል፤ እነሱ ደግሞ በተራቸው ለሂታውያን ነገሥታትና ለሶርያ ነገሥታት ሁሉ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ይሸጡ ነበር።
-