ዘዳግም 17:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 አምላክህ ይሖዋ የሚመርጠውን ንጉሥ ታነግሣለህ። የምታነግሠውም ንጉሥ ከወንድሞችህ መካከል መሆን ይኖርበታል።+ ወንድምህ ያልሆነን ባዕድ ሰው በላይህ ላይ ማንገሥ አይገባህም። 16 ይሁን እንጂ ንጉሡ ለራሱ ፈረሶች ማብዛት+ ወይም የፈረሶቹን ቁጥር ለመጨመር ሲል ሕዝቡ ወደ ግብፅ እንዲመለስ ማድረግ የለበትም፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ‘በዚህ መንገድ ፈጽሞ ዳግመኛ እንዳትመለሱ’ ብሏችኋል። 1 ነገሥት 4:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 ሰለሞን ሠረገሎቹን ለሚጎትቱት ፈረሶች የሚሆኑ 4,000* ጋጣዎችና 12,000 ፈረሶች* ነበሩት።+
15 አምላክህ ይሖዋ የሚመርጠውን ንጉሥ ታነግሣለህ። የምታነግሠውም ንጉሥ ከወንድሞችህ መካከል መሆን ይኖርበታል።+ ወንድምህ ያልሆነን ባዕድ ሰው በላይህ ላይ ማንገሥ አይገባህም። 16 ይሁን እንጂ ንጉሡ ለራሱ ፈረሶች ማብዛት+ ወይም የፈረሶቹን ቁጥር ለመጨመር ሲል ሕዝቡ ወደ ግብፅ እንዲመለስ ማድረግ የለበትም፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ‘በዚህ መንገድ ፈጽሞ ዳግመኛ እንዳትመለሱ’ ብሏችኋል።