2 ሳሙኤል 7:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ+ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ከአብራክህ የሚወጣውን ዘርህን አስነሳለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።+ 13 ለስሜ የሚሆን ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ።+ 1 ዜና መዋዕል 22:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 እነሆ፣ የሰላም* ሰው የሚሆን ወንድ ልጅ ትወልዳለህ፤+ በዙሪያውም ካሉት ጠላቶቹ በሙሉ እረፍት እሰጠዋለሁ፤+ ስሙ ሰለሞን*+ ይባላልና፤ በእሱም ዘመን ለእስራኤል ሰላምና ጸጥታ እሰጣለሁ።+ 10 ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው።+ እሱ ልጄ ይሆናል፤ እኔም አባቱ እሆናለሁ።+ የንግሥናውን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።’+ 2 ዜና መዋዕል 2:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እነሆ፣ በፊቱ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን+ ለማጠን፣ የሚነባበረውን ዳቦ*+ ዘወትር በዚያ ለማስቀመጥ እንዲሁም በየጠዋቱና በየማታው፣+ በየሰንበቱ፣+ በየወር መባቻውና+ በአምላካችን በይሖዋ የበዓላት ወቅቶች+ የሚቃጠል መባ ለማቅረብ ለአምላኬ ለይሖዋ ስም ቤት ልሠራና ለእሱ ልቀድሰው አስቤአለሁ። ይህም እስራኤላውያን ሁልጊዜ ሊፈጽሙት የሚገባ ግዴታ ነው።
12 የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ+ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ከአብራክህ የሚወጣውን ዘርህን አስነሳለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።+ 13 ለስሜ የሚሆን ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ።+
9 እነሆ፣ የሰላም* ሰው የሚሆን ወንድ ልጅ ትወልዳለህ፤+ በዙሪያውም ካሉት ጠላቶቹ በሙሉ እረፍት እሰጠዋለሁ፤+ ስሙ ሰለሞን*+ ይባላልና፤ በእሱም ዘመን ለእስራኤል ሰላምና ጸጥታ እሰጣለሁ።+ 10 ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው።+ እሱ ልጄ ይሆናል፤ እኔም አባቱ እሆናለሁ።+ የንግሥናውን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።’+
4 እነሆ፣ በፊቱ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን+ ለማጠን፣ የሚነባበረውን ዳቦ*+ ዘወትር በዚያ ለማስቀመጥ እንዲሁም በየጠዋቱና በየማታው፣+ በየሰንበቱ፣+ በየወር መባቻውና+ በአምላካችን በይሖዋ የበዓላት ወቅቶች+ የሚቃጠል መባ ለማቅረብ ለአምላኬ ለይሖዋ ስም ቤት ልሠራና ለእሱ ልቀድሰው አስቤአለሁ። ይህም እስራኤላውያን ሁልጊዜ ሊፈጽሙት የሚገባ ግዴታ ነው።