የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 49:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 ሴሎ* እስኪመጣ ድረስ በትረ መንግሥት ከይሁዳ፣+ የአዛዥም በትር ከእግሮቹ መካከል አይወጣም፤+ ለእሱም ሕዝቦች ይታዘዙለታል።+

  • 1 ነገሥት 8:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 ይሖዋ የገባውን ቃል ፈጽሟል፤ ልክ ይሖዋ ቃል በገባው መሠረት አባቴን ዳዊትን ተክቼ በእስራኤል ዙፋን ላይ ተቀምጫለሁና። በተጨማሪም ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ስም ቤት ሠርቻለሁ፤+

  • 1 ዜና መዋዕል 17:11-14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 “ ‘ “የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ ከአባቶችህ ጋር ለመሆን በምትሄድበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ዘርህን ይኸውም ከወንዶች ልጆችህ መካከል አንዱን አስነሳለሁ፤+ ንግሥናውንም አጸናለሁ።+ 12 ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም ዙፋኑን ለዘላለም አጸናለሁ።+ 13 አባት እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል።+ ታማኝ ፍቅሬንም ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንደወሰድኩ+ ከእሱ ላይ አልወስድም።+ 14 በቤቴና በንጉሣዊ ግዛቴ ላይ ለዘላለም ጸንቶ እንዲኖር አደርገዋለሁ፤+ ዙፋኑም ለዘላለም ይዘልቃል።” ’ ”+

  • መዝሙር 132:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ይሖዋ ለዳዊት ምሏል፤

      የገባውን ቃል ፈጽሞ አያጥፍም፦

      “ከዘሮችህ መካከል አንዱን*

      በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።+

  • ኢሳይያስ 9:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  7 በዳዊት ዙፋንና+ በመንግሥቱ ላይ ይቀመጣል፤

      እየተጠናከረ የሚሄደው አገዛዙም* ሆነ

      ሰላሙ ፍጻሜ አይኖረውም።+

      ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም

      በማይናወጥ ሁኔታ ይመሠረታል፤+

      በፍትሕና+ በጽድቅም+ ጸንቶ ይኖራል።

      የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቅንዓት ይህን ያደርጋል።

  • ኢሳይያስ 11:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ከእሴይ+ ጉቶ፣ ቅርንጫፍ ይወጣል፤

      ከሥሮቹም የሚወጣው ቀንበጥ ፍሬ ያፈራል።+

  • ማቴዎስ 21:9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 በተጨማሪም ከፊት ከፊቱ የሚሄደውና ከኋላው የሚከተለው ሕዝብ “የዳዊትን ልጅ እንድታድነው እንለምንሃለን!*+ በይሖዋ* ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!+ በሰማይ የምትኖረው ሆይ፣ እንድታድነው እንለምንሃለን!”+ ብሎ ይጮኽ ነበር።

  • ማቴዎስ 22:42
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 42 “ስለ መሲሑ* ምን ትላላችሁ? የማን ልጅ ነው?” እነሱም “የዳዊት” አሉት።+

  • ሉቃስ 1:32, 33
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 32 እሱም ታላቅ ይሆናል፤+ የልዑሉም አምላክ ልጅ ይባላል፤+ ይሖዋ* አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤+ 33 በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።”+

  • ዮሐንስ 7:42
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 42 ቅዱስ መጽሐፉ ክርስቶስ ከዳዊት ዘርና+ ዳዊት ከኖረበት መንደር+ ከቤተልሔም+ እንደሚመጣ ይናገር የለም?”

  • የሐዋርያት ሥራ 2:30
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 30 እሱ ነቢይ ስለነበረና አምላክ ከዘሮቹ አንዱን* በዙፋኑ ላይ እንደሚያስቀምጥ በመሐላ ቃል እንደገባለት ስላወቀ+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ