-
2 ዜና መዋዕል 4:18-22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 ሰለሞን የሠራቸው ዕቃዎች እጅግ ብዙ ነበሩ፤ የመዳቡም ክብደት ምን ያህል እንደሆነ አልታወቀም።+
19 ሰለሞን ለእውነተኛው አምላክ ቤት መገልገያ የሚሆኑትን የሚከተሉትን ነገሮች+ ሠራ፦ የወርቅ መሠዊያውን፣+ ገጸ ኅብስቱ የሚቀመጥባቸውን+ ጠረጴዛዎች፣+ 20 በመመሪያው መሠረት በውስጠኛው ክፍል ፊት የሚበሩትን ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መቅረዞችና መብራቶቻቸውን፣+ 21 ከወርቅ ይኸውም እጅግ ከጠራ ወርቅ የተሠሩትን የፈኩ አበቦች፣ መብራቶችና መቆንጠጫዎች፣ 22 ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩትን የእሳት ማጥፊያዎች፣ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ ጽዋዎችና መኮስተሪያዎች እንዲሁም ከወርቅ የተሠሩትን የቤቱን መግቢያ፣ የቅድስተ ቅዱሳኑን+ የውስጥ በሮችና የቤተ መቅደሱን ቤት በሮች።+
-