-
1 ነገሥት 7:48-50አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
48 ሰለሞንም ለይሖዋ ቤት መገልገያ የሚሆኑትን የሚከተሉትን ነገሮች ሠራ፦ የወርቅ መሠዊያውን፣+ ገጸ ኅብስት የሚቀመጥበትን የወርቅ ጠረጴዛ፣+ 49 በውስጠኛው ክፍል ፊት በቀኝና በግራ የሚቀመጡትን ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ+ አምስት አምስት መቅረዞች፣+ ከወርቅ የተሠሩትን የፈኩ አበቦች፣+ መብራቶችና መቆንጠጫዎች፣ 50 ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩትን ሳህኖች፣ የእሳት ማጥፊያዎች፣+ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ ጽዋዎችና+ መኮስተሪያዎች+ እንዲሁም ከወርቅ የተሠሩትን የውስጠኛው ክፍል+ ማለትም የቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችና የመቅደሱ በሮች+ የሚሽከረከሩባቸውን መቆሚያዎች።
-