1 ነገሥት 9:27, 28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ኪራምም ከሰለሞን አገልጋዮች ጋር አብረው እንዲሠሩ አገልጋዮቹን ይኸውም ልምድ ያላቸውን ባሕረኞች ከእነዚህ መርከቦች ጋር ላከ።+ 28 እነሱም ወደ ኦፊር+ በመሄድ 420 ታላንት ወርቅ አምጥተው ለንጉሥ ሰለሞን ሰጡት። መዝሙር 45:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ከተከበሩት እመቤቶችህ መካከል የነገሥታት ልጆች ይገኛሉ። እቴጌይቱ* በኦፊር ወርቅ+ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች።
27 ኪራምም ከሰለሞን አገልጋዮች ጋር አብረው እንዲሠሩ አገልጋዮቹን ይኸውም ልምድ ያላቸውን ባሕረኞች ከእነዚህ መርከቦች ጋር ላከ።+ 28 እነሱም ወደ ኦፊር+ በመሄድ 420 ታላንት ወርቅ አምጥተው ለንጉሥ ሰለሞን ሰጡት።