ዘሌዋውያን 26:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 በከፍታ ቦታዎች ላይ ያሉትን ቅዱስ ስፍራዎቻችሁን+ አጠፋለሁ፤ የዕጣን ማጨሻዎቻችሁንም አስወግዳለሁ፤ በድናችሁንም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ* በድን ላይ እከምረዋለሁ፤+ እኔም ተጸይፌያችሁ ከእናንተ ዞር እላለሁ።*+ ዘኁልቁ 33:52 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 52 የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አባሯቸው፤ የተቀረጹ የድንጋይ ምስሎቻቸውንም+ ሁሉ አጥፉ፤ ከብረት የተሠሩ ሐውልቶቻቸውንም*+ በሙሉ አስወግዱ፤ በከፍታ ቦታዎች ላይ ያሉ ቅዱስ ስፍራዎቻቸውን+ ሁሉ አፍርሱ። 2 ነገሥት 21:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ምናሴ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 12 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ55 ዓመት ገዛ።+ የእናቱ ስም ሄፍጺባ ነበር። 2 ነገሥት 21:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 አባቱ ሕዝቅያስ አስወግዷቸው የነበሩትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች መልሶ ገነባ፤+ እንዲሁም የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ለባአል መሠዊያዎችን አቆመ፤+ የማምለኪያ ግንድም* ሠራ።+ ለሰማይ ሠራዊትም ሁሉ ሰገደ፤ እነሱንም አገለገለ።+
30 በከፍታ ቦታዎች ላይ ያሉትን ቅዱስ ስፍራዎቻችሁን+ አጠፋለሁ፤ የዕጣን ማጨሻዎቻችሁንም አስወግዳለሁ፤ በድናችሁንም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ* በድን ላይ እከምረዋለሁ፤+ እኔም ተጸይፌያችሁ ከእናንተ ዞር እላለሁ።*+
52 የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አባሯቸው፤ የተቀረጹ የድንጋይ ምስሎቻቸውንም+ ሁሉ አጥፉ፤ ከብረት የተሠሩ ሐውልቶቻቸውንም*+ በሙሉ አስወግዱ፤ በከፍታ ቦታዎች ላይ ያሉ ቅዱስ ስፍራዎቻቸውን+ ሁሉ አፍርሱ።
3 አባቱ ሕዝቅያስ አስወግዷቸው የነበሩትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች መልሶ ገነባ፤+ እንዲሁም የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ለባአል መሠዊያዎችን አቆመ፤+ የማምለኪያ ግንድም* ሠራ።+ ለሰማይ ሠራዊትም ሁሉ ሰገደ፤ እነሱንም አገለገለ።+