2 ሳሙኤል 8:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 የደማስቆዎቹ ሶርያውያን፣+ የጾባህን ንጉሥ ሃዳድኤዜርን ለመርዳት በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶርያውያን መካከል 22,000 ሰዎችን ገደለ።+ 1 ነገሥት 19:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “ወደ ደማስቆ ምድረ በዳ ተመልሰህ ሂድ። እዚያም ስትደርስ ሃዛኤልን+ በሶርያ ላይ ንጉሥ አድርገህ ቀባው። ኢሳይያስ 7:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 የሶርያ ራስ ደማስቆ፣የደማስቆ ራስ ደግሞ ረጺን ነውና። ኤፍሬም በ65 ዓመት ውስጥብትንትኑ ወጥቶ ሕዝብ መሆኑ ይቀራል።+