ዘኁልቁ 3:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ሹማቸው፤ እነሱም የክህነት ኃላፊነታቸውን ይወጡ፤+ ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው* ወደ መቅደሱ ቢቀርብ ይገደል።”+ 1 ነገሥት 13:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 ይህ ሁሉ ከሆነም በኋላ ቢሆን ኢዮርብዓም ከመጥፎ መንገዱ አልተመለሰም፤ ከዚህ ይልቅ ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ከሕዝቡ መካከል ካህናት መሾሙን ቀጠለ።+ እንዲሁም ካህን ለመሆን የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው “ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ካህን ይሁን” በማለት ይሾመው* ነበር።+ 2 ዜና መዋዕል 11:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ሌዋውያኑ የይሖዋ ካህናት ሆነው እንዳያገለግሉ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አባረዋቸው ስለነበር+ የግጦሽ መሬታቸውንና ርስታቸውን+ ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ነበር። 2 ዜና መዋዕል 13:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 የአሮን ዘሮች የሆኑትን የይሖዋን ካህናትና ሌዋውያንን አላባረራችሁም?+ ደግሞስ እንደ ሌሎቹ አገሮች ሕዝቦች የራሳችሁን ካህናት አልሾማችሁም?+ አንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ይዞ የሚመጣ ማንኛውም ሰው አማልክት ላልሆኑት ጣዖቶች ካህን መሆን ይችላል።
33 ይህ ሁሉ ከሆነም በኋላ ቢሆን ኢዮርብዓም ከመጥፎ መንገዱ አልተመለሰም፤ ከዚህ ይልቅ ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ከሕዝቡ መካከል ካህናት መሾሙን ቀጠለ።+ እንዲሁም ካህን ለመሆን የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው “ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ካህን ይሁን” በማለት ይሾመው* ነበር።+
14 ሌዋውያኑ የይሖዋ ካህናት ሆነው እንዳያገለግሉ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አባረዋቸው ስለነበር+ የግጦሽ መሬታቸውንና ርስታቸውን+ ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ነበር።
9 የአሮን ዘሮች የሆኑትን የይሖዋን ካህናትና ሌዋውያንን አላባረራችሁም?+ ደግሞስ እንደ ሌሎቹ አገሮች ሕዝቦች የራሳችሁን ካህናት አልሾማችሁም?+ አንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ይዞ የሚመጣ ማንኛውም ሰው አማልክት ላልሆኑት ጣዖቶች ካህን መሆን ይችላል።