1 ነገሥት 12:28-30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 በመሆኑም ንጉሡ ከተማከረ በኋላ ሁለት የወርቅ ጥጃዎችን+ ሠርቶ ሕዝቡን “ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት መንገላታት ይሆንባችኋል። እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይኸውልህ” አለ።+ 29 ከዚያም አንደኛውን በቤቴል+ ሌላኛውን ደግሞ በዳን+ አቆመው። 30 ይህም ለኃጢአት ዳረጋቸው፤+ ሕዝቡም በዳን የሚገኘውን ጥጃ ለማምለክ እስከዚያ ድረስ ይሄድ ነበር። 1 ነገሥት 13:33, 34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 ይህ ሁሉ ከሆነም በኋላ ቢሆን ኢዮርብዓም ከመጥፎ መንገዱ አልተመለሰም፤ ከዚህ ይልቅ ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ከሕዝቡ መካከል ካህናት መሾሙን ቀጠለ።+ እንዲሁም ካህን ለመሆን የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው “ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ካህን ይሁን” በማለት ይሾመው* ነበር።+ 34 ይህም ኃጢአት የኢዮርብዓም+ ቤት ከምድር ገጽ እንዲጠፋና እንዲደመሰስ ምክንያት ሆነ።+
28 በመሆኑም ንጉሡ ከተማከረ በኋላ ሁለት የወርቅ ጥጃዎችን+ ሠርቶ ሕዝቡን “ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት መንገላታት ይሆንባችኋል። እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይኸውልህ” አለ።+ 29 ከዚያም አንደኛውን በቤቴል+ ሌላኛውን ደግሞ በዳን+ አቆመው። 30 ይህም ለኃጢአት ዳረጋቸው፤+ ሕዝቡም በዳን የሚገኘውን ጥጃ ለማምለክ እስከዚያ ድረስ ይሄድ ነበር።
33 ይህ ሁሉ ከሆነም በኋላ ቢሆን ኢዮርብዓም ከመጥፎ መንገዱ አልተመለሰም፤ ከዚህ ይልቅ ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ከሕዝቡ መካከል ካህናት መሾሙን ቀጠለ።+ እንዲሁም ካህን ለመሆን የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው “ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ካህን ይሁን” በማለት ይሾመው* ነበር።+ 34 ይህም ኃጢአት የኢዮርብዓም+ ቤት ከምድር ገጽ እንዲጠፋና እንዲደመሰስ ምክንያት ሆነ።+