33 ሆኖም ለእሱ ታማኝ ፍቅር ማሳየቴን አልተውም፤+
የገባሁትንም ቃል አላጥፍም።
34 ቃል ኪዳኔን አላፈርስም፤+
ከአንደበቴ የወጣውንም ቃል አለውጥም።+
35 ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁ፤
ዳዊትን አልዋሸውም።+
36 ዘሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤+
ዙፋኑ በፊቴ እንዳለችው ፀሐይ ይጸናል።+
37 በሰማያት ታማኝ ምሥክር ሆና እንደምትኖረው እንደ ጨረቃ፣
ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” (ሴላ)