መሳፍንት 18:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 በተጨማሪም ከተማዋን ለእስራኤል በተወለደለት+ በአባታቸው በዳን ስም ዳን+ ብለው ጠሯት። የከተማዋ የቀድሞ ስም ግን ላይሽ ነበር።+ 1 ነገሥት 12:28, 29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 በመሆኑም ንጉሡ ከተማከረ በኋላ ሁለት የወርቅ ጥጃዎችን+ ሠርቶ ሕዝቡን “ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት መንገላታት ይሆንባችኋል። እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይኸውልህ” አለ።+ 29 ከዚያም አንደኛውን በቤቴል+ ሌላኛውን ደግሞ በዳን+ አቆመው።
28 በመሆኑም ንጉሡ ከተማከረ በኋላ ሁለት የወርቅ ጥጃዎችን+ ሠርቶ ሕዝቡን “ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት መንገላታት ይሆንባችኋል። እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይኸውልህ” አለ።+ 29 ከዚያም አንደኛውን በቤቴል+ ሌላኛውን ደግሞ በዳን+ አቆመው።