የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 32:39
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 39 እንግዲህ እኔ እሱ እንደሆንኩ እዩ፤+

      ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት የሉም።+

      እኔ እገድላለሁ፤ እኔ ሕያው አደርጋለሁ።+

      እኔ አቆስላለሁ፤+ እኔው እፈውሳለሁ፤+

      ከእጄም ማዳን የሚችል የለም።+

  • 1 ሳሙኤል 2:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  6 ይሖዋ ይገድላል፤ ሕይወትንም ያድናል፤*

      ወደ መቃብር* ያወርዳል፤ ከዚያም ያወጣል።+

  • 2 ነገሥት 4:32
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 32 ኤልሳዕ ወደ ቤት ሲገባ ልጁ ሞቶ በእሱ አልጋ ላይ ተጋድሞ አገኘው።+

  • 2 ነገሥት 4:34
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 34 ከዚያም አልጋው ላይ ወጥቶ ልጁ ላይ በመተኛት አፉን በአፉ፣ ዓይኑን በዓይኑ እንዲሁም መዳፉን በመዳፉ ላይ አድርጎ ላዩ ላይ ተደፋበት፤ የልጁም ሰውነት መሞቅ ጀመረ።+

  • 2 ነገሥት 13:21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 21 የተወሰኑ ሰዎች አንድ ሰው ሊቀብሩ ሲሉ ወራሪውን ቡድን ተመለከቱ፤ ስለዚህ ሰውየውን ኤልሳዕ የተቀበረበት ቦታ ውስጥ ወርውረው እየሮጡ ሄዱ። ሰውየውም የኤልሳዕን አፅም በነካ ጊዜ ሕያው ሆነ፤+ በእግሩም ቆመ።

  • ሉቃስ 7:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 የሞተውም ሰው ቀና ብሎ ተቀመጠና መናገር ጀመረ፤ ኢየሱስም ለእናቱ ሰጣት።+

  • ሉቃስ 8:54, 55
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 54 እሱ ግን እጇን በመያዝ ድምፁን ከፍ አድርጎ “አንቺ ልጅ፣ ተነሽ!” አለ።+ 55 የልጅቷም መንፈስ*+ ተመለሰ፤ ወዲያውም ተነሳች፤+ የምትበላውም ነገር እንዲሰጧት አዘዘ።

  • ዮሐንስ 5:28, 29
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 በዚህ አትደነቁ፤ በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣልና፤+ 29 መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩ* ደግሞ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ።+

  • ዮሐንስ 11:44
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 44 የሞተው ሰው እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደተገነዙ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ ተጠምጥሞ ነበር። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ” አላቸው።

  • የሐዋርያት ሥራ 9:40, 41
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 40 ጴጥሮስም ሁሉም እንዲወጡ ካደረገ በኋላ+ ተንበርክኮ ጸለየ። ከዚያም ወደ አስከሬኑ ዞር ብሎ “ጣቢታ፣ ተነሽ!” አለ። እሷም ዓይኖቿን ገለጠች፤ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ቀና ብላ ተቀመጠች።+ 41 እሱም እጇን ይዞ አስነሳት፤ ቅዱሳኑንና መበለቶቹንም ጠርቶ ሕያው መሆኗን አሳያቸው።+

  • የሐዋርያት ሥራ 20:9, 10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ጳውሎስ ንግግሩን ባስረዘመ ጊዜ መስኮት ላይ ተቀምጦ የነበረ አውጤኪስ የሚባል አንድ ወጣት ከባድ እንቅልፍ ያዘው፤ እንቅልፍ ስለጣለውም ከሁለተኛ ፎቅ ላይ ወደቀ፤ ሲያነሱትም ሞቶ ነበር። 10 ጳውሎስም ከፎቅ ላይ ወርዶ በላዩ ላይ ተኝቶ አቀፈውና+ “በሕይወት ስላለ አትንጫጩ”* አላቸው።+

  • ሮም 14:9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ክርስቶስ የሞተውና ዳግም ሕያው የሆነው ለዚህ ዓላማ ይኸውም በሙታንም ሆነ በሕያዋን ላይ ጌታ ይሆን ዘንድ ነውና።+

  • ዕብራውያን 11:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 አብርሃም በተፈተነ ጊዜ+ ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ እስከ ማቅረብ ድረስ እምነት አሳይቷል፤ የተስፋን ቃል በደስታ የተቀበለው ይህ ሰው አንድያ ልጁን መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ተዘጋጅቶ ነበር፤+

  • ዕብራውያን 11:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 ይሁንና አምላክ ከሞት እንኳ ሳይቀር ሊያስነሳው እንደሚችል ተገንዝቦ ነበር፤ ልጁንም ከሞት አፋፍ መልሶ አገኘው፤ ይህም እንደ ምሳሌ ሆኖ አገልግሏል።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ