ዘዳግም 32:39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 39 እንግዲህ እኔ እሱ እንደሆንኩ እዩ፤+ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት የሉም።+ እኔ እገድላለሁ፤ እኔ ሕያው አደርጋለሁ።+ እኔ አቆስላለሁ፤+ እኔው እፈውሳለሁ፤+ከእጄም ማዳን የሚችል የለም።+ ኢዮብ 14:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ምነው በመቃብር* ውስጥ በሰወርከኝ!+ቁጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግከኝ!ቀጠሮም ሰጥተህ ባስታወስከኝ!+ መዝሙር 30:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ይሖዋ ሆይ፣ ከመቃብር* አውጥተኸኛል።*+ በሕይወት አቆይተኸኛል፤ ወደ ጉድጓድ* ከመውረድ አድነኸኛል።+ መዝሙር 49:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ሆኖም አምላክ ከመቃብር* እጅ ይዋጀኛል፤*+እሱ ይይዘኛልና። (ሴላ) መዝሙር 68:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 እውነተኛው አምላክ፣ አዳኝ አምላካችን ነው፤+ደግሞም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ከሞት ይታደጋል።+ ሆሴዕ 13:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ከመቃብር* እጅ እዋጃቸዋለሁ፤ከሞትም እታደጋቸዋለሁ።+ ሞት ሆይ፣ መንደፊያህ የት አለ?+ መቃብር ሆይ፣ አጥፊነትህ የት አለ?+ ርኅራኄ ከዓይኔ ፊት ይሰወራል። ዮሐንስ 11:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ማርታም “በመጨረሻው ቀን በትንሣኤ እንደሚነሳ አውቃለሁ” አለችው።+ 1 ቆሮንቶስ 15:55 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 55 “ሞት ሆይ፣ ድል አድራጊነትህ የት አለ? ሞት ሆይ፣ መንደፊያህ የት አለ?”+
39 እንግዲህ እኔ እሱ እንደሆንኩ እዩ፤+ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት የሉም።+ እኔ እገድላለሁ፤ እኔ ሕያው አደርጋለሁ።+ እኔ አቆስላለሁ፤+ እኔው እፈውሳለሁ፤+ከእጄም ማዳን የሚችል የለም።+
14 ከመቃብር* እጅ እዋጃቸዋለሁ፤ከሞትም እታደጋቸዋለሁ።+ ሞት ሆይ፣ መንደፊያህ የት አለ?+ መቃብር ሆይ፣ አጥፊነትህ የት አለ?+ ርኅራኄ ከዓይኔ ፊት ይሰወራል።