የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 9:1-3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ከዚያም ነቢዩ ኤልሳዕ ከነቢያት ልጆች አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ልብስህን በወገብህ ታጠቅና ይህን የዘይት ዕቃ ይዘህ ወደ ራሞትጊልያድ+ በፍጥነት ሂድ። 2 እዚያም ስትደርስ የኒምሺን ልጅ፣ የኢዮሳፍጥን ልጅ ኢዩን+ ፈልገው፤ ከዚያም ገብተህ ከወንድሞቹ መካከል አስነሳውና ወደ ውስጠኛው ክፍል ውሰደው። 3 የዘይቱንም ዕቃ ወስደህ ዘይቱን በራሱ ላይ አፍስ፤ እንዲህም በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንተን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጌ ቀብቼሃለሁ።”’+ ከዚያም በሩን ከፍተህ በፍጥነት ሽሽ።”

  • 2 ነገሥት 9:30-33
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 30 ከዚያም ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል+ መጣ፤ ኤልዛቤልም+ ይህን ሰማች። በመሆኑም ዓይኖቿን ተኩላና ፀጉሯን አሰማምራ በመስኮት ቁልቁል ትመለከት ጀመር። 31 ኢዩም በቅጥሩ በር በኩል ሲገባ ኤልዛቤል “ጌታውን የገደለው ዚምሪ ምን እንደደረሰበት አታውቅም?” አለችው።+ 32 እሱም ወደ መስኮቱ ቀና ብሎ በመመልከት “ከእኔ ጎን የቆመ ማን ነው? ማን ነው?”+ አለ። ወዲያውኑ ሁለት ወይም ሦስት የሚሆኑ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት ቁልቁል ተመለከቱት። 33 እሱም “ወደ ታች ወርውሯት!” አላቸው። እነሱም ወረወሯት፤ ደሟም በግድግዳውና በፈረሶቹ ላይ ተረጨ፤ ኢዩም በፈረሶቹ ረጋገጣት።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ