-
1 ነገሥት 16:15-19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ27ኛው ዓመት፣ ሠራዊቱ የፍልስጤማውያን የሆነችውን ጊበቶንን+ ከቦ በነበረበት ወቅት ዚምሪ በቲርጻ ለሰባት ቀን ነገሠ። 16 በኋላም ከተማዋን ከቦ የነበረው ሠራዊት “ዚምሪ ሴራ በመጠንሰስ ንጉሡን ገድሎታል” የሚል ወሬ ሰማ። በመሆኑም መላው እስራኤል የሠራዊቱ አለቃ የሆነውን ኦምሪን+ በዚያን ቀን በሰፈሩ ውስጥ በእስራኤል ላይ አነገሡት። 17 ኦምሪና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከጊበቶን ወጥተው ቲርጻን ከበቡ። 18 ዚምሪም ከተማዋ መያዟን ሲያይ በንጉሡ ቤት* ወዳለው የማይደፈር ማማ ገብቶ በውስጡ እንዳለ ቤቱን በእሳት አቃጠለው፤ በዚህም የተነሳ ሞተ።+ 19 ይህም የሆነው የኢዮርብዓምን መንገድ በመከተል በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በመፈጸም በሠራው በገዛ ኃጢአቱና እስራኤላውያን እንዲሠሩ ባደረገው ኃጢአት የተነሳ ነው።+
-