2 ሳሙኤል 15:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 አቢሴሎምም “የቀንደ መለከት ድምፅ ስትሰሙ ‘አቢሴሎም በኬብሮን ነገሠ!’+ ብላችሁ አውጁ” በማለት በመላው የእስራኤል ነገዶች መካከል ሰላዮችን አሰማራ። 1 ነገሥት 1:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ይቀቡታል፤+ ከዚያም ቀንደ መለከት እየነፋችሁ ‘ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር!’+ በሉ። 1 ነገሥት 1:39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 39 ካህኑ ሳዶቅም ከድንኳኑ+ ውስጥ የዘይቱን ቀንድ+ ወስዶ ሰለሞንን ቀባው፤+ እነሱም ቀንደ መለከት መንፋት ጀመሩ፤ ሕዝቡም ሁሉ “ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር!” እያለ ይጮኽ ጀመር።
39 ካህኑ ሳዶቅም ከድንኳኑ+ ውስጥ የዘይቱን ቀንድ+ ወስዶ ሰለሞንን ቀባው፤+ እነሱም ቀንደ መለከት መንፋት ጀመሩ፤ ሕዝቡም ሁሉ “ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር!” እያለ ይጮኽ ጀመር።