ዘፀአት 3:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “በግብፅ የሚኖረውን የሕዝቤን መከራ በእርግጥ አይቻለሁ፤ አስገድደው በሚያሠሯቸው ሰዎች የተነሳ የሚያሰሙትን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ እየደረሰባቸው ያለውንም ሥቃይ በሚገባ አውቃለሁ።+ መሳፍንት 10:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 እነሱም ከመካከላቸው ባዕዳን አማልክትን አስወግደው ይሖዋን አገለገሉ፤+ በመሆኑም በእስራኤል ላይ እየደረሰ የነበረውን መከራ ሊታገሥ አልቻለም።* + 2 ነገሥት 14:26, 27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 ይሖዋ በእስራኤል ላይ እየደረሰ ያለውን ከባድ ሥቃይ ተመልክቶ ነበርና።+ በዚያም እስራኤልን ሌላው ቀርቶ ምስኪኑንና ደካማውን የሚረዳ አልነበረም። 27 ሆኖም ይሖዋ የእስራኤልን ስም ከሰማይ በታች ጠራርጎ እንደማያጠፋ ቃል ገብቶ ነበር።+ በመሆኑም በኢዮዓስ ልጅ በኢዮርብዓም አማካኝነት አዳናቸው።+
7 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “በግብፅ የሚኖረውን የሕዝቤን መከራ በእርግጥ አይቻለሁ፤ አስገድደው በሚያሠሯቸው ሰዎች የተነሳ የሚያሰሙትን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ እየደረሰባቸው ያለውንም ሥቃይ በሚገባ አውቃለሁ።+
26 ይሖዋ በእስራኤል ላይ እየደረሰ ያለውን ከባድ ሥቃይ ተመልክቶ ነበርና።+ በዚያም እስራኤልን ሌላው ቀርቶ ምስኪኑንና ደካማውን የሚረዳ አልነበረም። 27 ሆኖም ይሖዋ የእስራኤልን ስም ከሰማይ በታች ጠራርጎ እንደማያጠፋ ቃል ገብቶ ነበር።+ በመሆኑም በኢዮዓስ ልጅ በኢዮርብዓም አማካኝነት አዳናቸው።+