-
2 ነገሥት 18:9-11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ሕዝቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ማለትም የእስራኤል ንጉሥ የኤላህ ልጅ ሆሺአ+ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰልምናሶር በሰማርያ ላይ ዘምቶ ከበባት።+ 10 በሦስተኛው ዓመት ማብቂያ ላይ ከተማዋን ያዟት፤+ ሕዝቅያስ በነገሠ በስድስተኛው ዓመት ይኸውም የእስራኤል ንጉሥ ሆሺአ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰማርያ ተያዘች። 11 ከዚያም የአሦር ንጉሥ እስራኤላውያንን ወደ አሦር በግዞት ወስዶ+ በሃላህ፣ በጎዛን ወንዝ አጠገብ በምትገኘው በሃቦርና በሜዶናውያን ከተሞች አሰፈራቸው።+
-