-
2 ነገሥት 17:3-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 የአሦር ንጉሥ ሰልምናሶር በእሱ ላይ መጣ፤+ ሆሺአም አገልጋዩ ሆነ፤ ገበረለትም።+ 4 ሆኖም የአሦር ንጉሥ ሰልምናሶር ሆሺአ እንዳሴረበት አወቀ፤ ምክንያቱም ሆሺአ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሶህ መልእክተኞች ልኮ ነበር፤+ ደግሞም ቀደም ባሉት ዓመታት ያደርግ እንደነበረው ለአሦር ንጉሥ መገበሩን አቁሞ ነበር። ስለሆነም የአሦር ንጉሥ እስር ቤት ውስጥ አስሮ አስቀመጠው።
5 የአሦር ንጉሥ መላ አገሪቱን ወረረ፤ ወደ ሰማርያም መጥቶ ከተማዋን ለሦስት ዓመት ከበባት። 6 ሆሺአ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ያዘ።+ ከዚያም የእስራኤልን ሕዝብ ወደ አሦር በግዞት+ በመውሰድ በሃላህ፣ በጎዛን+ ወንዝ አጠገብ በምትገኘው በሃቦርና በሜዶናውያን ከተሞች አሰፈራቸው።+
-