-
ኢሳይያስ 37:14-20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ሕዝቅያስ ደብዳቤዎቹን ከመልእክተኞቹ እጅ ተቀብሎ አነበበ። ከዚያም ወደ ይሖዋ ቤት ወጥቶ ደብዳቤዎቹን* በይሖዋ ፊት ዘረጋ።+ 15 ሕዝቅያስም ወደ ይሖዋ እንዲህ ሲል ጸለየ፦+ 16 “ከኪሩቤል በላይ* የምትቀመጥ፣ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣+ የምድር መንግሥታት ሁሉ እውነተኛ አምላክ አንተ ብቻ ነህ። ሰማያትንና ምድርን ሠርተሃል። 17 ይሖዋ ሆይ፣ ጆሮህን አዘንብለህ ስማ!+ ይሖዋ ሆይ፣ ዓይንህን ገልጠህ እይ!+ ሰናክሬም ሕያው የሆነውን አምላክ ለማቃለል የላከውን ቃል ሁሉ ስማ።+ 18 ይሖዋ ሆይ፣ የአሦር ነገሥታት ሌሎቹን አገሮች ሁሉና የገዛ ራሳቸውን ምድር እንዳጠፉ አይካድም።+ 19 አማልክታቸውንም እሳት ውስጥ ጨምረዋል፤+ ምክንያቱም የሰው እጅ ሥራ፣ እንጨትና ድንጋይ እንጂ አማልክት አይደሉም።+ ሊያጠፏቸው የቻሉት በዚህ ምክንያት ነው። 20 አሁን ግን አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ የምድር መንግሥታት ሁሉ፣ አንተ ብቻ እውነተኛ አምላክ እንደሆንክ ያውቁ ዘንድ ይሖዋ ሆይ፣ ከእጁ አድነን።”+
-