የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 9:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ንጉሥ ሰለሞን የይሖዋን ቤት፣+ የራሱን ቤት፣* ጉብታውን፣*+ የኢየሩሳሌምን ቅጥር፣ ሃጾርን፣+ መጊዶንና+ ጌዜርን+ እንዲገነቡ ስለመለመላቸው የግዳጅ ሥራ የሚሠሩ ሠራተኞች+ የሚገልጸው ዘገባ ይህ ነው።

  • 2 ዜና መዋዕል 35:20-25
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 ከዚህ ሁሉ በኋላ ኢዮስያስ ቤተ መቅደሱን* አዘጋጅቶ ባጠናቀቀ ጊዜ የግብፁ ንጉሥ ኒካዑ+ በኤፍራጥስ አጠገብ ባለው በካርከሚሽ ለመዋጋት መጣ። በዚህ ጊዜ ኢዮስያስ ሊገጥመው ወጣ።+ 21 ኒካዑም እንዲህ ሲል መልእክተኞችን ላከበት፦ “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፣ እኔን ልትወጋ የመጣኸው ለምንድን ነው? አሁን የመጣሁት ከሌላ ብሔር ጋር ልዋጋ እንጂ አንተን ልወጋ አይደለም፤ አምላክም እንድፈጥን አዞኛል። ከእኔ ጋር የሆነውን አምላክ መቃወም ቢቀርብህ ይሻላል፤ አለዚያ ያጠፋሃል።” 22 ኢዮስያስ ግን ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም፤ ይልቁንም ማንነቱ እንዳይታወቅ ራሱን ለውጦ+ ከእሱ ጋር ለመዋጋት ወጣ፤ በኒካዑ በኩል የተነገረውን የአምላክ ቃል አልሰማም። በመሆኑም ለመዋጋት ወደ መጊዶ+ ሜዳ መጣ።

      23 ቀስተኞችም ንጉሥ ኢዮስያስን ወጉት፤ ንጉሡም አገልጋዮቹን “ክፉኛ ስለቆሰልኩ ከዚህ አውጡኝ” አላቸው። 24 በመሆኑም አገልጋዮቹ ከሠረገላው አውርደው በሁለተኛው የጦር ሠረገላው ላይ ካስቀመጡት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት። እሱም በዚህ ሁኔታ ሞተ፤ በአባቶቹም መቃብር ተቀበረ፤+ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሁሉ ለኢዮስያስ አለቀሱ። 25 ኤርምያስም+ ለኢዮስያስ የሐዘን እንጉርጉሮ ተቀኘ፤ ወንዶችና ሴቶች ዘማሪዎችም+ ሁሉ እስከ ዛሬ ድረስ በሙሿቸው* ላይ ስለ ኢዮስያስ ይዘምራሉ፤ ደግሞም በእስራኤል እንዲዘመርና ሌሎች ሙሾዎች በተጻፉበት መጽሐፍ ላይ እንዲሰፍር ተወሰነ።

  • ዘካርያስ 12:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 በዚያን ቀን በኢየሩሳሌም የሚለቀሰው ለቅሶ በመጊዶ ሜዳ፣ በሃዳድሪሞን እንደተለቀሰው ለቅሶ ታላቅ ይሆናል።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ