የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 36:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ሴዴቅያስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 21 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ11 ዓመት ገዛ።+

  • 2 ዜና መዋዕል 36:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ደግሞም በአምላክ ስም ባስማለው በንጉሥ ናቡከደነጾር ላይ ዓመፀ፤+ ግትር ሆነ፤* ልቡንም አጠነከረ፤ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ ይሖዋ ለመመለስ አሻፈረኝ አለ።

  • ኤርምያስ 27:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም+ ተመሳሳይ ነገር ነገርኩት፤ እንዲህም አልኩት፦ “አንገታችሁን በባቢሎን ንጉሥ ቀንበር ሥር አስገቡ፤ እሱንና ሕዝቡንም አገልግሉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።+

  • ኤርምያስ 38:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 ከዚያም ኤርምያስ ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለባቢሎን ንጉሥ መኳንንት እጅህን ብትሰጥ* ሕይወትህ ትተርፋለች፤* ይህችም ከተማ በእሳት አትቃጠልም፤ አንተም ሆንክ ቤተሰብህ በሕይወት ትተርፋላችሁ።+

  • ሕዝቅኤል 17:12-15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 “እባክህ፣ ለዓመፀኛው ቤት ይህን ተናገር፦ ‘የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አትገነዘቡም?’ እንዲህ በል፦ ‘እነሆ፣ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ንጉሥዋንና መኳንንቷን ማረከ፤ ወደ ባቢሎንም ይዟቸው ተመለሰ።+ 13 በተጨማሪም ከንጉሣውያን ዘር አንዱን ወስዶ+ ከእሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ በመሐላም ቃል አስገባው።+ ከዚያም የምድሪቱን ታላላቅ ሰዎች ወሰደ፤+ 14 ይህም መንግሥቲቱ ዝቅ እንድትልና ማንሰራራት እንዳትችል እንዲሁም የእሱን ቃል ኪዳን በመጠበቅ ብቻ እንድትኖር ለማድረግ ነው።+ 15 ንጉሡ ግን በመጨረሻ ፈረሶችና+ ብዙ ሠራዊት እንዲልኩለት መልእክተኞቹን ወደ ግብፅ በመስደድ+ በእሱ ላይ ዓመፀ።+ ታዲያ ይሳካለት ይሆን? እነዚህን ነገሮች ያደረገው ከቅጣት ያመልጣል? ቃል ኪዳኑንስ አፍርሶ ማምለጥ ይችላል?’+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ