2 ነገሥት 24:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፣ ከአገልጋዮቹ፣ ከመኳንንቱና ከቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ+ ጋር ሆኖ ወደ ባቢሎን ንጉሥ+ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ዮአኪንን ማርኮ ወሰደው።+ 2 ነገሥት 24:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ኢየሩሳሌምን በሙሉ፣ መኳንንቱን በሙሉ፣+ ኃያላን ተዋጊዎቹን ሁሉ፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችንና አንጥረኞችን*+ በአጠቃላይ 10,000 ሰዎችን በግዞት ወሰደ። በጣም ድሃ ከሆኑት የምድሪቱ ነዋሪዎች በስተቀር በዚያ የቀረ አልነበረም።+ ኢሳይያስ 39:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ‘ከአንተ ከሚወለዱት ከገዛ ልጆችህ መካከልም አንዳንዶቹ ይወሰዳሉ፤ በባቢሎን ንጉሥ ቤተ መንግሥትም ባለሥልጣናት ይሆናሉ።’”+ ኤርምያስ 22:24, 25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ይሖዋ፣ ‘አንተ የይሁዳ ንጉሥ፣ የኢዮዓቄም+ ልጅ፣ ኮንያሁ*+ በቀኝ እጄ እንዳለ የማኅተም ቀለበት ብትሆን እንኳ ከዚያ አውጥቼ እጥልሃለሁ! 25 ሕይወትህን ለማጥፋት በሚሹ* ሰዎች እጅ፣ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅና በከለዳውያን እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ።+ ኤርምያስ 52:31, 32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ ኤዊልሜሮዳክ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን+ ፈታው፤* ከእስር ቤትም አወጣው፤+ ይህም የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በግዞት በተወሰደ በ37ኛው ዓመት፣ በ12ኛው ወር፣ ከወሩም በ25ኛው ቀን ነበር። 32 በርኅራኄም አናገረው፤ ዙፋኑንም በባቢሎን ከእሱ ጋር ከነበሩት ከሌሎች ነገሥታት ዙፋን ይበልጥ ከፍ ከፍ አደረገለት።
12 የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፣ ከአገልጋዮቹ፣ ከመኳንንቱና ከቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ+ ጋር ሆኖ ወደ ባቢሎን ንጉሥ+ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ዮአኪንን ማርኮ ወሰደው።+
14 ኢየሩሳሌምን በሙሉ፣ መኳንንቱን በሙሉ፣+ ኃያላን ተዋጊዎቹን ሁሉ፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችንና አንጥረኞችን*+ በአጠቃላይ 10,000 ሰዎችን በግዞት ወሰደ። በጣም ድሃ ከሆኑት የምድሪቱ ነዋሪዎች በስተቀር በዚያ የቀረ አልነበረም።+
24 “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ይሖዋ፣ ‘አንተ የይሁዳ ንጉሥ፣ የኢዮዓቄም+ ልጅ፣ ኮንያሁ*+ በቀኝ እጄ እንዳለ የማኅተም ቀለበት ብትሆን እንኳ ከዚያ አውጥቼ እጥልሃለሁ! 25 ሕይወትህን ለማጥፋት በሚሹ* ሰዎች እጅ፣ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅና በከለዳውያን እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ።+
31 ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ ኤዊልሜሮዳክ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን+ ፈታው፤* ከእስር ቤትም አወጣው፤+ ይህም የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በግዞት በተወሰደ በ37ኛው ዓመት፣ በ12ኛው ወር፣ ከወሩም በ25ኛው ቀን ነበር። 32 በርኅራኄም አናገረው፤ ዙፋኑንም በባቢሎን ከእሱ ጋር ከነበሩት ከሌሎች ነገሥታት ዙፋን ይበልጥ ከፍ ከፍ አደረገለት።