የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 29:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  3 አንቺን ለማጥቃት በዙሪያሽ እሰፍራለሁ፤

      በሹል እንጨት አጥርሻለሁ፤

      በአንቺም ዙሪያ ቅጥር እገነባለሁ።+

  • ኤርምያስ 32:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤርምያስም በይሁዳ ንጉሥ ቤት፣* በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ታስሮ ነበር።

  • ኤርምያስ 32:28
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ይህችን ከተማ ለከለዳውያንና ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር* እሰጣታለሁ፤ እሱም ይይዛታል።+

  • ኤርምያስ 39:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 39 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾርና* መላው ሠራዊቱ መጥተው ኢየሩሳሌምን ከበቧት።+

  • ኤርምያስ 52:4, 5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ሠራዊቱን ሁሉ አስከትሎ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ። በዙሪያዋም ሰፈሩ፤ ደግሞም በዙሪያዋ የአፈር ቁልል ቆለሉ።+ 5 ከተማዋም እስከ ንጉሥ ሴዴቅያስ 11ኛ ዓመት ድረስ ተከበበች።

  • ሕዝቅኤል 4:1, 2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ አንድ ጡብ ወስደህ በፊትህ አስቀምጥ። በላዩም ላይ የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅረጽበት። 2 ከተማዋን ክበብ፤+ ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ሥራባት፤+ የአፈር ቁልል ደልድልባት፤+ የጦር ሰፈሮችን ሥራባት እንዲሁም በዙሪያዋ የመደርመሻ መሣሪያዎችን ደግንባት።+

  • ሕዝቅኤል 21:21, 22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 21 የባቢሎን ንጉሥ ያሟርት ዘንድ በመንታ መንገድ ይኸውም በሁለቱ መንገዶች መገንጠያ ላይ ይቆማልና። ፍላጾችን ይወዘውዛል። ጣዖቶቹን* ያማክራል፤ ጉበት ይመረምራል። 22 በቀኝ እጁ የወጣው ሟርት የመደርመሻ መሣሪያዎችን ለመደገን፣ የግድያ ትእዛዝ ለማስተላለፍ፣ የጦርነት ሁካታ ለማሰማት፣ በበሮቿ ላይ የመደርመሻ መሣሪያዎች ለመደገን፣ በዙሪያዋ የአፈር ቁልል ለመደልደልና ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ለመሥራት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ አመለከተው።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ