የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 29
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኢሳይያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ለአርዔል ወዮላት! (1-16)

        • ‘በከንፈሩ ያከብረኛል’ (13)

      • መስማት የተሳናቸው ይሰማሉ፤ ዓይነ ስውራኑም ያያሉ (17-24)

ኢሳይያስ 29:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “የአምላክ የመሠዊያ ምድጃ” የሚል ትርጉም ሊኖረው ይችላል፤ ኢየሩሳሌምን የሚያመለክት ይመስላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 5:7, 9
  • +ዘዳ 16:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 296-297

ኢሳይያስ 29:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:53-55
  • +ኢሳ 51:19፤ ሰቆ 1:4
  • +ኤር 15:14፤ ሶፎ 1:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 296-297

ኢሳይያስ 29:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:11፤ 25:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 296-297

ኢሳይያስ 29:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 51:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 296-297

ኢሳይያስ 29:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የባዕዳን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 13:19፤ 14:22፤ 21:9
  • +ኢሳ 13:11፤ 17:13
  • +ኢሳ 47:9፤ 48:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 297

ኢሳይያስ 29:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 2:10፤ ኤር 50:25፤ ናሆም 1:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 297

ኢሳይያስ 29:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 25:12, 14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 297-298

ኢሳይያስ 29:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሱ ባዶ እንደምትሆን።”

  • *

    ወይም “ነፍሱ በጥም እንደምትቃጠል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 10:12፤ ኤር 51:24

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 297-298

ኢሳይያስ 29:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕን 1:5
  • +ኢሳ 6:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 298-299

ኢሳይያስ 29:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 6:10፤ ሮም 11:8
  • +ኤር 14:14፤ 27:15
  • +ሚክ 3:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 298-299

ኢሳይያስ 29:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 8:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 298-299

ኢሳይያስ 29:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 298-299

ኢሳይያስ 29:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 48:1፤ ኤር 5:2
  • +ማቴ 15:7-9፤ ማር 7:6-8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 299, 301

ኢሳይያስ 29:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 28:21፤ ዕን 1:5
  • +ኤር 8:9፤ 1ቆሮ 1:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 299

ኢሳይያስ 29:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ምክራቸውን ከይሖዋ ለመሰወር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 30:1
  • +ሕዝ 8:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 299-300

ኢሳይያስ 29:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እንዴት ጠማሞች ናችሁ!”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 64:8
  • +ኤር 18:6
  • +ሮም 9:20, 21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 301

ኢሳይያስ 29:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 35:1፤ 41:19
  • +ኢሳ 32:14, 15

ኢሳይያስ 29:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 35:5፤ 42:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!፣ ገጽ 232-233, 235

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 298, 300

ኢሳይያስ 29:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 41:16

ኢሳይያስ 29:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚክ 2:1

ኢሳይያስ 29:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወቀሳ በሚሰነዝረው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +አሞጽ 5:10
  • +ሕዝ 13:19

ኢሳይያስ 29:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ውርደትና ኀፍረት እንደማይደርስበት ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 9:7፤ ሚክ 7:20
  • +ኢዩ 2:27

ኢሳይያስ 29:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለእስራኤልም አምላክ አክብሮታዊ ፍርሃት ያሳያሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 45:11
  • +ኢሳ 8:13፤ ሆሴዕ 3:5

ኢሳይያስ 29:24

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 301

ተዛማጅ ሐሳብ

ኢሳ. 29:12ሳሙ 5:7, 9
ኢሳ. 29:1ዘዳ 16:16
ኢሳ. 29:2ዘዳ 28:53-55
ኢሳ. 29:2ኢሳ 51:19፤ ሰቆ 1:4
ኢሳ. 29:2ኤር 15:14፤ ሶፎ 1:7
ኢሳ. 29:32ነገ 24:11፤ 25:1
ኢሳ. 29:4ኢሳ 51:23
ኢሳ. 29:5ኢሳ 13:19፤ 14:22፤ 21:9
ኢሳ. 29:5ኢሳ 13:11፤ 17:13
ኢሳ. 29:5ኢሳ 47:9፤ 48:3
ኢሳ. 29:61ሳሙ 2:10፤ ኤር 50:25፤ ናሆም 1:3
ኢሳ. 29:7ኤር 25:12, 14
ኢሳ. 29:8ኢሳ 10:12፤ ኤር 51:24
ኢሳ. 29:9ዕን 1:5
ኢሳ. 29:9ኢሳ 6:9
ኢሳ. 29:10ኢሳ 6:10፤ ሮም 11:8
ኢሳ. 29:10ኤር 14:14፤ 27:15
ኢሳ. 29:10ሚክ 3:7
ኢሳ. 29:11ኢሳ 8:16
ኢሳ. 29:13ኢሳ 48:1፤ ኤር 5:2
ኢሳ. 29:13ማቴ 15:7-9፤ ማር 7:6-8
ኢሳ. 29:14ኢሳ 28:21፤ ዕን 1:5
ኢሳ. 29:14ኤር 8:9፤ 1ቆሮ 1:19
ኢሳ. 29:15ኢሳ 30:1
ኢሳ. 29:15ሕዝ 8:12
ኢሳ. 29:16ኢሳ 64:8
ኢሳ. 29:16ኤር 18:6
ኢሳ. 29:16ሮም 9:20, 21
ኢሳ. 29:17ኢሳ 35:1፤ 41:19
ኢሳ. 29:17ኢሳ 32:14, 15
ኢሳ. 29:18ኢሳ 35:5፤ 42:16
ኢሳ. 29:19ኢሳ 41:16
ኢሳ. 29:20ሚክ 2:1
ኢሳ. 29:21አሞጽ 5:10
ኢሳ. 29:21ሕዝ 13:19
ኢሳ. 29:22ነህ 9:7፤ ሚክ 7:20
ኢሳ. 29:22ኢዩ 2:27
ኢሳ. 29:23ኢሳ 45:11
ኢሳ. 29:23ኢሳ 8:13፤ ሆሴዕ 3:5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኢሳይያስ 29:1-24

ኢሳይያስ

29 “ለአርዔል፣* ዳዊት ለሰፈረባት ከተማ+ ለአርዔል ወዮላት!

በዓመት ላይ ዓመት ጨምሩ፤

ዓመታዊ በዓሎቻችሁን+ ማክበራችሁን ቀጥሉ።

 2 እኔ ግን በአርዔል ላይ የሚያስጨንቅ ነገር አመጣለሁ፤+

ለቅሶና ዋይታም ይሆናል፤+

እሷም ለእኔ፣ እንደ አምላክ የመሠዊያ ምድጃ ትሆናለች።+

 3 አንቺን ለማጥቃት በዙሪያሽ እሰፍራለሁ፤

በሹል እንጨት አጥርሻለሁ፤

በአንቺም ዙሪያ ቅጥር እገነባለሁ።+

 4 ትወድቂያለሽ፤ ትዋረጃለሽም፤

መሬት ላይ ሆነሽ ትናገሪያለሽ፤

የምትናገሪው ነገር በአፈር ይታፈናል።

ድምፅሽ እንደ መናፍስት ጠሪ ድምፅ

ከመሬት ይመጣል፤+

ቃልሽም ከአፈር ይጮኻል።

 5 የጠላቶችሽ* ሠራዊት እንደላመ ዱቄት ይሆናል፤+

የጨቋኞች መንጋ ተጠርጎ እንደሚሄድ ገለባ ይሆናል።+

ይህም ሳይታሰብ፣ በቅጽበት ይፈጸማል።+

 6 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ትኩረቱን ወደ አንቺ በማዞር

በነጎድጓድ፣ በምድር መናወጥ፣ በታላቅ ድምፅ፣

በውሽንፍር፣ በአውሎ ነፋስና በሚባላ የእሳት ነበልባል ያድንሻል።”+

 7 በዚያን ጊዜ አርዔልን የሚወጉ የብሔራት ሠራዊት ሁሉ፣+

ይኸውም ጦርነት የሚከፍቱባት ሁሉ፣

በእሷ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ማማዎችን የሚሠሩና

ጭንቀት ላይ የሚጥሏት ሁሉ

እንደ ሕልም፣ በሌሊትም እንደሚታይ ራእይ ይሆናሉ።

 8 አዎ፣ የተራበ ሰው በሕልሙ ሲበላ ቆይቶ

ሲነቃ ግን ረሃቡ እንደማይለቀው* ሁሉ፣

ደግሞም የተጠማ ሰው በሕልሙ ሲጠጣ ቆይቶ

ሲነቃ ግን ዝሎና ተጠምቶ እንደሚነሳ* ሁሉ እንዲሁ ይሆናል።

በጽዮን ተራራ ላይ ጦርነት የሚከፍቱ የብሔራት ሠራዊትም ሁሉ

ተመሳሳይ ነገር ይደርስባቸዋል።+

 9 ክው በሉ፤ ተደነቁም፤+

ዓይናችሁን ጨፍኑ፤ ዕውሮችም ሁኑ።+

በወይን ጠጅ አይሁን እንጂ ሰክረዋል፤

በሚያሰክር መጠጥ አይሁን እንጂ ተንገዳግደዋል።

10 ይሖዋ ኃይለኛ የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋልና፤+

ዓይኖቻችሁን ይኸውም ነቢያትን ጨፍኖባችኋል፤+

ራሶቻችሁን ይኸውም ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል።+

11 የሁሉ ነገር ራእይ እንደታሸገ መጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል።+ መጽሐፉን ማንበብ ለሚችል ሰው “እባክህ፣ ጮክ ብለህ አንብበው” ብለው ሲሰጡት “ታሽጓልና አልችልም” ይላል። 12 መጽሐፉንም ማንበብ ለማይችል ሰው “እባክህ፣ ይህን አንብበው” ብለው ሲሰጡት “ፈጽሞ ማንበብ አልችልም” ይላል።

13 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ ወደ እኔ የሚቀርበው በአፉ ብቻ ነው፤

በከንፈሩም ያከብረኛል፤+

ልቡ ግን ከእኔ እጅግ የራቀ ነው፤

እኔንም የሚፈራው፣ ሰዎች ያስተማሩትን ትእዛዛት በማክበር ነው።+

14 ስለዚህ እኔ በእነዚህ ሰዎች ላይ ዳግመኛ የሚያስደንቁ ነገሮች አደርጋለሁ፤+

በድንቅ ላይ ድንቅ ነገር እፈጽማለሁ፤

የጥበበኞቻቸውም ጥበብ ይጠፋል፤

የአስተዋዮቻቸውም ማስተዋል ይሰወራል።”+

15 ዕቅዳቸውን ከይሖዋ ለመሰወር* ከፍተኛ ጥረት ለሚያደርጉ ወዮላቸው!+

“ማን ያየናል?

ማንስ ያውቅብናል?” በማለት

ተግባራቸውን በጨለማ ቦታ ያከናውናሉ።+

16 እናንተ ሰዎች፣ ነገር ታጣምማላችሁ!*

ሸክላ ሠሪው እንደ ሸክላው ሊቆጠር ይገባል?+

የተሠራው ነገር ስለ ሠሪው

“እሱ አልሠራኝም” ማለቱ ተገቢ ነው?+

ደግሞስ ዕቃው ሠሪውን

“ማስተዋል የለውም” ይላል?+

17 በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊባኖስ ወደ ፍራፍሬ እርሻነት ይለወጣል፤+

የፍራፍሬ እርሻውም እንደ ጫካ ይቆጠራል።+

18 በዚያ ቀን፣ መስማት የተሳናቸው ሰዎች የመጽሐፉን ቃል ይሰማሉ፤

የዓይነ ስውራኑም ዓይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተላቀው ያያሉ።+

19 የዋሆች በይሖዋ እጅግ ሐሴት ያደርጋሉ፤

በሰዎች መካከል ያሉ ድሆችም በእስራኤል ቅዱስ ደስ ይላቸዋል።+

20 ጨቋኙ ያከትምለታልና፤

ጉረኛውም ያበቃለታል፤

ሌሎችን ለመጉዳት አሰፍስፈው የሚጠባበቁ ሁሉ ይጠፋሉ፤+

21 ሌሎችን በውሸት ቃል በደለኛ የሚያደርጉ፣

በከተማዋ በር፣+ በተሟጋቹ* ላይ ወጥመድ የሚዘረጉና

መሠረተ ቢስ በሆነ ክስ ጻድቁን ሰው ፍትሕ የሚነፍጉ ይጠፋሉ።+

22 ስለዚህ አብርሃምን+ የተቤዠው ይሖዋ ለያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፦

“ያዕቆብ ከእንግዲህ አያፍርም፤

ፊቱም ከእንግዲህ አይገረጣም።*+

23 የእጆቼ ሥራ የሆኑትን ልጆቹን

በመካከሉ በሚያይበት ጊዜ፣+

ስሜን ይቀድሳሉና፤

አዎ፣ የያዕቆብን ቅዱስ ይቀድሳሉ፤

የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ።*+

24 በመንፈስ የባዘኑ ማስተዋል ያገኛሉ፤

የሚያጉረመርሙም የሚሰጣቸውን ትምህርት ይቀበላሉ።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ