1 ነገሥት 9:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ይህም ቤት የፍርስራሽ ክምር ይሆናል።+ በዚያም የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ በመገረም ትኩር ብለው እየተመለከቱ ‘ይሖዋ በዚህች ምድርና በዚህ ቤት ላይ እንዲህ ያለ ነገር ያደረገው ለምንድን ነው?’+ በማለት ያፏጫሉ። መዝሙር 74:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ለዘለቄታው ወደፈራረሰው ቦታ አቅና።+ ጠላት በቅዱሱ ስፍራ ያለውን ነገር ሁሉ አጥፍቷል።+ መዝሙር 79:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 79 አምላክ ሆይ፣ ብሔራት ርስትህን+ ወረውታል፤ቅዱስ መቅደስህንም አርክሰዋል፤+ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር አድርገዋታል።+ ኢሳይያስ 64:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 አባቶቻችን አንተን ያወደሱበትየቅድስናና የክብር ቤታችን*በእሳት ተቃጥሏል፤+ከፍ አድርገን እንመለከታቸው የነበሩት ነገሮች በሙሉ ፈራርሰዋል። ኤርምያስ 7:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግኩት ሁሉ በስሜ በተጠራው፣+ እናንተም በምትታመኑበት በዚህ ቤት+ ላይ እንዲሁም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጠሁት በዚህ ቦታ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።+ ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ጠላት በውድ ሀብቶቿ ሁሉ ላይ እጁን አሳርፏል።+ ወደ አንተ ጉባኤ እንዳይገቡ ያዘዝካቸው ብሔራትወደ መቅደሷ ሲገቡ አይታለችና።+ ሰቆቃወ ኤርምያስ 2:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋ መሠዊያውን ናቀ፤መቅደሱን ተወ።+ የማይደፈሩ ማማዎቿን ግንቦች ለጠላት አሳልፎ ሰጠ።+ በበዓል ቀን እንደሚደረገው ሁሉ በይሖዋ ቤት በታላቅ ድምፅ ጮኹ።+ ሚክያስ 3:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ስለዚህ በእናንተ የተነሳጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤+የቤቱም* ተራራ፣ በጫካ እንዳሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች* ይሆናል።+
8 ይህም ቤት የፍርስራሽ ክምር ይሆናል።+ በዚያም የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ በመገረም ትኩር ብለው እየተመለከቱ ‘ይሖዋ በዚህች ምድርና በዚህ ቤት ላይ እንዲህ ያለ ነገር ያደረገው ለምንድን ነው?’+ በማለት ያፏጫሉ።
14 ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግኩት ሁሉ በስሜ በተጠራው፣+ እናንተም በምትታመኑበት በዚህ ቤት+ ላይ እንዲሁም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጠሁት በዚህ ቦታ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።+
7 ይሖዋ መሠዊያውን ናቀ፤መቅደሱን ተወ።+ የማይደፈሩ ማማዎቿን ግንቦች ለጠላት አሳልፎ ሰጠ።+ በበዓል ቀን እንደሚደረገው ሁሉ በይሖዋ ቤት በታላቅ ድምፅ ጮኹ።+