-
2 ሳሙኤል 13:28አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
28 ከዚያም አቢሴሎም አገልጋዮቹን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፣ እኔም አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሞቅ ሲለው ‘አምኖንን ምቱት!’ እላችኋለሁ። እናንተም ትገድሉታላችሁ። አትፍሩ፤ የማዛችሁ እኔ አይደለሁም? በርቱ! ደፋሮች ሁኑ!”
-
-
2 ሳሙኤል 13:37አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
37 አቢሴሎም ግን ኮብልሎ የገሹር ንጉሥ ወደሆነው ወደ አሚሁድ ልጅ ወደ ታልማይ+ ሄደ። ዳዊትም ለልጁ ብዙ ቀናት አለቀሰ።
-
-
2 ሳሙኤል 18:14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ኢዮዓብም “ከዚህ በላይ ከአንተ ጋር ጊዜ አላጠፋም!” አለው። ከዚያም ሦስት ቀስቶች* ይዞ በመሄድ አቢሴሎም በትልቁ ዛፍ መሃል ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ ቀስቶቹን ልቡ ላይ ሰካቸው።
-