ዘፍጥረት 29:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 አሁንም ደግሞ ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “ሦስት ወንዶች ልጆች ስለወለድኩለት አሁን ባሌ ይቀርበኛል” አለች። በዚህም የተነሳ ሌዊ*+ ተባለ። ዘፀአት 6:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 የሌዊ+ ወንዶች ልጆች በየቤተሰብ የዘር ሐረጋቸው ስማቸው ይህ ነው፦ ጌድሶን፣ ቀአት እና ሜራሪ።+ ሌዊ 137 ዓመት ኖረ።