የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ሳሙኤል 5:6-10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 ዳዊትና ሰዎቹም በምድሪቱ የሚኖሩትን ኢያቡሳውያን+ ለመውጋት ወደ ኢየሩሳሌም ዘመቱ። እነሱም ዳዊትን “ፈጽሞ ወደዚህ አትገባም! ዕውሮችና ሽባዎች እንኳ ያባርሩሃል” በማለት ተሳለቁበት። ይህን ያሉት ‘ዳዊት ፈጽሞ ወደዚህ አይገባም’ ብለው ስላሰቡ ነበር።+ 7 ይሁን እንጂ ዳዊት በአሁኑ ጊዜ የዳዊት ከተማ+ ተብላ የምትጠራውን የጽዮንን ምሽግ ያዘ። 8 ስለሆነም በዚያን ቀን ዳዊት “በኢያቡሳውያን ላይ ጥቃት የሚሰነዝር ማንኛውም ሰው ዳዊት የሚጠላቸውን* ‘ሽባዎችንና ዕውሮችን’ ለመምታት በውኃ መውረጃው ቦይ በኩል ማለፍ አለበት!” አለ። “ዕውርና ሽባ ፈጽሞ ወደ ቤት አይገቡም” የሚባለውም በዚህ የተነሳ ነው። 9 ከዚያም ዳዊት በምሽጉ ውስጥ መኖር ጀመረ፤ ስፍራውም የዳዊት ከተማ ተብሎ ይጠራ ነበር፤* እሱም ከጉብታው*+ አንስቶ ወደ ውስጥ ዙሪያውን መገንባት ጀመረ።+ 10 በዚህ ሁኔታ ዳዊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ ሄደ፤+ የሠራዊት አምላክ ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ