4 በኋላም ዳዊትና መላው እስራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ይኸውም ኢያቡሳውያን+ ይኖሩበት ወደነበረው ምድር ወደ ኢያቡስ+ ሄዱ። 5 የኢያቡስ ነዋሪዎችም ዳዊትን “ፈጽሞ ወደዚህ አትገባም!” በማለት ተሳለቁበት።+ ይሁን እንጂ ዳዊት በአሁኑ ጊዜ የዳዊት ከተማ+ ተብላ የምትጠራውን የጽዮንን+ ምሽግ ያዘ። 6 ስለሆነም ዳዊት “ኢያቡሳውያንን በመጀመሪያ የሚመታ ሰው አለቃና መኮንን ይሆናል” አለ። የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ+ በመጀመሪያ ወደዚያ ወጣ፤ እሱም አለቃ ሆነ።