ዘዳግም 4:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 “እዚያ ሆናችሁ አምላካችሁን ይሖዋን ብትፈልጉት፣ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ*+ ብትሹት በእርግጥ ታገኙታላችሁ።+ 2 ዜና መዋዕል 20:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ኢዮሳፍጥ ይህን ሲሰማ ፈራ፤ ይሖዋንም ለመፈለግ ቆርጦ ተነሳ።*+ በመሆኑም በመላው ይሁዳ ጾም አወጀ። ዳንኤል 9:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በመሆኑም ወደ እውነተኛው አምላክ ወደ ይሖዋ ፊቴን አዞርኩ፤ ማቅ ለብሼና በራሴ ላይ አመድ ነስንሼ በጸሎትና በጾም ተማጸንኩት።+