ዘፍጥረት 49:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሴሎ* እስኪመጣ ድረስ በትረ መንግሥት ከይሁዳ፣+ የአዛዥም በትር ከእግሮቹ መካከል አይወጣም፤+ ለእሱም ሕዝቦች ይታዘዙለታል።+ 1 ዜና መዋዕል 5:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሁዳ+ ከወንድሞቹ የሚበልጥ ከመሆኑም ሌላ መሪ+ የሚሆነው የተገኘው ከእሱ ነው፤ ሆኖም የብኩርና መብቱን ያገኘው ዮሴፍ ነበር። መዝሙር 60:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ጊልያድም ሆነ ምናሴ የእኔ ናቸው፤+ኤፍሬምም የራስ ቁሬ ነው፤*ይሁዳ በትረ መንግሥቴ ነው።+