11 በመጨረሻም ሳሙኤል እሴይን “ወንዶች ልጆችህ እነዚሁ ብቻ ናቸው?” አለው። እሱም “ታናሽየው+ ገና ይቀራል፤ በጎች እየጠበቀ ነው” አለ።+ ከዚያም ሳሙኤል እሴይን “በል ልከህ አስመጣው፤ ምክንያቱም እሱ ሳይመጣ ምግብ ለመብላት መቀመጥ አንችልም” አለው። 12 በመሆኑም ልኮ አስመጣው። እሱም የቀይ ዳማ፣ ዓይኑ የሚያምርና መልከ መልካም ነበር።+ ከዚያም ይሖዋ “ተነስ፣ ቀባው፤ የመረጥኩት እሱን ነው!” አለው።+