1 ሳሙኤል 17:45 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 45 ዳዊትም መልሶ ፍልስጤማዊውን እንዲህ አለው፦ “አንተ ሰይፍ፣ ጭሬና ጦር+ ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን አንተ በተሳለቅክበት፣+ የእስራኤል ተዋጊዎች አምላክ በሆነው በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ስም+ እመጣብሃለሁ። መዝሙር 20:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በማዳን ሥራህ በደስታ እልል እንላለን፤+በአምላካችን ስም ዓርማችንን ወደ ላይ ከፍ እናደርጋለን።+ ይሖዋ የለመንከውን ሁሉ ይፈጽምልህ። ምሳሌ 18:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 የይሖዋ ስም ጽኑ ግንብ ነው።+ ጻድቅ ወደዚያ በመሮጥ ጥበቃ ያገኛል።*+
45 ዳዊትም መልሶ ፍልስጤማዊውን እንዲህ አለው፦ “አንተ ሰይፍ፣ ጭሬና ጦር+ ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን አንተ በተሳለቅክበት፣+ የእስራኤል ተዋጊዎች አምላክ በሆነው በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ስም+ እመጣብሃለሁ።