የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 7:13, 14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ንጉሥ ሰለሞን መልእክተኛ ልኮ ኪራምን+ ከጢሮስ አስመጣው። 14 ኪራም ከንፍታሌም ነገድ የሆነች የአንዲት መበለት ልጅ ነበር፤ አባቱ የጢሮስ ሰው ሲሆን የመዳብ ሥራ ባለሙያ+ ነበር፤ ኪራም ከማንኛውም የመዳብ* ሥራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችሎታ፣ ማስተዋልና+ ልምድ ነበረው። በመሆኑም ወደ ንጉሥ ሰለሞን መጥቶ ሥራዎቹን ሁሉ አከናወነለት።

  • 2 ዜና መዋዕል 4:11-16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 በተጨማሪም ኪራም አመድ ማጠራቀሚያዎቹን፣ አካፋዎቹንና ጎድጓዳ ሳህኖቹን ሠራ።+

      ኪራምም በእውነተኛው አምላክ ቤት ለንጉሥ ሰለሞን ያከናውን የነበረውን ሥራ ጨረሰ፤+ 12 ሁለቱን ዓምዶች፣+ በሁለቱ ዓምዶች አናት ላይ የነበሩትን የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸው የዓምድ ራሶች፣ በዓምዶቹ አናት ላይ የነበሩትን የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸውን ሁለቱን ክብ የዓምድ ራሶች የሚያስጌጡትን ሁለት መረቦች፣+ 13 ለሁለቱ መረቦች የተሠሩትን 400 ሮማኖች+ ማለትም በዓምዶቹ አናት ላይ የነበሩትን የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸውን ሁለት የዓምድ ራሶች ለማስጌጥ የተሠሩትን በእያንዳንዱ መረብ ላይ በሁለት ረድፍ የተደረደሩትን ሮማኖች፣+ 14 አሥሩን ጋሪዎችና* በጋሪዎቹ ላይ የነበሩትን አሥር የውኃ ገንዳዎች፣+ 15 ባሕሩንና ከሥሩ የነበሩትን 12 በሬዎች፣+ 16 አመድ ማጠራቀሚያዎቹን፣ አካፋዎቹን፣ ሹካዎቹንና+ ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ዕቃዎች ሁሉ ኪራምአቢቭ+ ለይሖዋ ቤት መገልገያ እንዲሆኑ ለንጉሥ ሰለሞን ከተወለወለ መዳብ ሠራ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ